በአለም አቀፍ የድፕሎማሲ መንደር ለውጥ እየታየ ይመስላል፡፡ በአገር ውስጥ ተቃውሞና ውግዘት እያስተናገደ ያለው የኢት/ያ መንግስት ሰሞኑን በአውሮፓ ህብረት በኩል ተጨማሪ ቢጫ
ካርድ ተመዞበታል፡፡ africannews የተሰኘ የዜና አውታር እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳዮችና
የፀጥታ ፓሊሲ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት Federica Mogherini ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ
ባስተላለፋት መልዕክት የኢትዮጵያ መንግስት በህገ መንግስቱ ላይ ያሰፈራቸውን ድሞክራሲያዊ እና ሰብዓዊ መብቶች
እንዲያከብር ጠይቀዋል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት የህብረቱ ተወካይ የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጭምር ሲሆኑ
አሳታፊ የሆነ የፓለቲካ ድርድር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማካሄድ ፍላጎት እንዳለና ይሄ ድርድር ደግሞ የራሱ የሆነ
የፓለቲካ ምህዳር ይጠይቃል ሲሉ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚጥለውን ገደብ አውግዘዋል፡፡ ("...there was the
need to initiate an inclusive political dialogue within the shortest
possible time. The dialogue ‘‘will require space, not restriction...")
ይህ የህብረቱ አቋም የሚያሳየው የኢት/ያ መንግስት አለም አቀፍ ተቀባይነት አደጋ ላይ እንደወደቀ ነው፡፡ በኢትዮጵያውያን ላይ ዘግናኝ የሆነ ግፍ ሲፈፀም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ አምባገነኖችን ሳይኮንን የቆየው አለም አቀፉ ማህበረሰብ አሁን ላይ እየነቃ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ አሳስቧቸው ወደ ኢት/ያ መመልከታቸው መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለም ሌሎች የአለም መንግስታት ተመሳሳይ አቋም ሊያራምዱ እንደሚችሉ ግልፅ ነው፡፡ በዚሁ ሰሞን የልዕለ ሀያሏ አገረ አሜሪካ የፌደራል መንግስት የህግ አውጭ ምክር ቤት ወይም ኮንግረንስ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወሳል፡፡ ይህ በውሳኔ ቁጥር 128 (Resolution No 128) መሰረት የወጣው መግለጫ ገዥውን መንግስት የሚያስጠነቅቅ ሀይለ ቃልም አለበት፡፡ እንግዲህ የአውሮፓ ህብረቱ ማሳሰቢያ ለኢህአዴግ ሌላ በእንቅርት ላይ ጆሮ ገድፍ መሆኑ ነው፡፡ የህብረቱ ተወካይ ግልፀኝነት የተሞላበት አሰራር ማስፈን ያስፈልጋል በማለት የኢት/ያን መንግስት በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንግስት የዜጎችን ቅሬታ ለመፍታት ቆርጦ ሊነሳ ይገባልም ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳይመንት ነው በማለት ለሀይለ ማርያም መናገራቸው ኢህአዴግ በአለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ እንከን እየገጠመውና ድጋፍ እየተነፈገ መሆኑን ያሳብቃል፡፡ ህብረቱ በተወካይቷ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት የተዘጋውን የፓለቲካ ምህዳር እንድከፍትና የዜጎችን መሰረታዊ ነፃነቶች እንድያከብር አሳስቧል፡፡ ("She further underlined the need for transparency and determined engagement by the government to respond to the grievances of the population. The EU said it expected the opening up of the democratic space, and respect of fundamental freedoms.")
ሁለቱ መሪዎች በቀጥታ ስልክ ጭምር የተነጋገሩ ሲሆን ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁም ተወያይተዋል፡፡ በህብረቱ በኩል አዋጁ የድሞክራሲ መርሆዎችና የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል የሚል ስጋት የቀረበ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት አይጋፋም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ ("The EU chief expressed concern over the curfew imposed on October 9 and its possible effect on democratic principles and civil rights of citizens. The Prime Minister on his part assured that the state of emergency will not breach human rights protected by the Ethiopian constitution").
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ማስተባበያቸው የነገሩን መንግስታቸው ከሀድ እንደሆነ ነው፡፡ እውነታው ግን በአገሪቱ ውስጥ ግልፅ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፍትህ እጦት መኖሩ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የፓለቲካ እስረኞች ቁጥርና በገፍ ህይወታቸውን የሚያጡት ዜጎች መበራከታቸው ጭምር ነው፡፡ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ ያለለምንም ህጋዊ ቅድመ ሁኔታ ዜጎችን ለእስር እየዳረ ያለ ስርዓት ሰብዓዊ መብት አክባሪ ነኝ ሲል እጅጉን ያሳፍራል፡፡
በስተመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምርጫ ህጉን የማሻሻል ስራ ተጀምሯል ያሉትን መረጃ መሰረት በማድረግ ህብረቱ አስፈላጊ የሆኑ የፓለቲካ ማሻሻያዎች ካልተደረጉ የታሰበው ነገር አላማውን እንደማያሳካ አረጋግጧል፡፡
ዋናው ጉዳይ የኢህአዴግ መንግስት አለም አቀፍ ቅቡልነቱን እያጣ መሆኑ ነው፡፡ ስርዓቱ የሚሻሻል እንዳልሆነ ቢታወቅም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያውያን ላይ ኢህአዴግ እያደረሰ ያለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መገንዘቡ ይበል ያሰኛል፡፡
በደርብ ተፈራ
Facebook address፦ https://www.facebook.com/teferaderbeee

No comments:
Post a Comment