In Ethiopia, Power is a short cut to get rich.
እውነታው ይህ ነው! ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ስልጣን ህዝብን ማገልገያ ሳይሆን ሀብት ቁንጮ ላይ ለመድረስ አቋራጭ ነው፡፡ ራስ ወዳድነት የባለስልጣኖቻችን መገለጫ ሆኗል፡፡ እስኪ ማነው "እኔ የአገር ሀብት አልነካሁም ንፁህ ነኝ የሚል ፃድቅ ባለስልጣን?" ሁሉም በሚባል ደረጃ በሙስና ተጨማልቀዋል፡፡ ገለልተኛ የሆነ አካል ጉዳዩን ቢያጣራው የሁሉም ጉድ ይወጣ ነበር፡፡ ታድያ ምን ዋጋ አለው! ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሳይቀር ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው፡፡ ኮሚሽኑ እከሌ ላይ ምርመራ ይጀመር የሚል ትዕዛዝ ከምኒልክ ቤተመንግስት ካልመጣለት ዘረፋ ሲካሄድ እያየ ጆሮ ዳባ ልበስ ነው የሚለው፡፡
የኛ ባለስልጣኖች ሆዳም ስለሆኑ የአገሪቱን ሀብት ብቻ በልተው አይጠግቡም፡፡ ዜጎችንም ከምድሯ ያጠፋሉ አሁንም እያደረጉት ያለው ነገር ይህ ነው፡፡
በተደጋጋሚ በፌስቡክ ገፄ ላይ ስላችሁ እንደነበረው በአገራችን ኢትዮጵያ ሙስና ተዘርቶ የሚበቅልበት ለም የሆነ የማህበረሰብ ባህል አለ፡፡
ሲሾም ያልበላ፤
ሲሻር ይቆጨዋል፡፡
ይህ አባባል የማንም አይደለም የኛው ነው፡፡ ባለስልጣናት ያገኙትን ወርቃማ አጋጣሚ ተጠቅመው የአገር ሃብትና ንብረትን ቢዘርፉ ችግሩ የእነሱ ብቻ ሳይሆን ያሳደጋቸው ማህበረሰብም ጭምር ነው፡፡ መንግስታዊ ሌቦችን የወለደው ማህበረሰብ ስርቆቱ ለሚያስከትለው ምጣኔ ሐብታዊ እና ሌሎች አገራዊ ቀውሶች ተጠያቂ ነው፡፡ እንደኛ ማህበረሰብ አንተ ተሿሚ ከሆንክ ወንበሯ ላይ እስካለህ ድረስ ጠንክረህ መዝረፍ አለብህ፡፡ ይህ ካልሆነ ወንበሩን ያጣኸው ቀን ይቆጭሀል፡፡ ሙስና እና ብልሹ አሰራር ተዘርቶ ቡቃያው የለመለመበት ምቹ የማህበረሰብ ባህል የት ነው ያለው ብሎ ለሚጠይቅ አድራሻው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ቢባል መሳሳት አይሆንም፡፡ የኛ ማህበረሰብ ‹‹የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ›› እያለ ዝርፊያን ያበረታታል፡፡ ለዘራፊዎችም ድጋፉን ይሰጣል፡፡ አብረህም እንድትዘርፍ ነፃነት ይሰጥሀል፡፡ ከዛ ልማታዊ ሌባ የሚል ታፔላ ይለጠፍብሀል፡፡
ሁሉም በየፊናው የአገር ሃብትን ከመዘበረ አገራዊ የገንዘብ ካዝናችን ባዶ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ኬንያውያን ‹‹አሁን ተራው የእኛ ነው›› የሚሉት አባባል ነበራቸው፡፡ አንድ ጎሳ ስልጣን ላይ ከወጣ የድርሻውን አንስቶ ይወርዳል፡፡ በእነሱ ባህል ስልጣን እጅህ ውስጥ ከገባ ዘረፋው ያንተ ተራ ነውና የድርሻህን ማንሳት አለብህ፡፡ ሩቅ ሳንሄድ እኛም አገር እየሆነ ያለው ነገር ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡
ሙስናን መዋጋት መጥፎ ባህልን ከማስወገድ መጀመር አለበት ብየ አምናለሁ፡፡ የሰው ልጅ ያደገበትን አካባቢ ይመስላል፡፡ የምንኖርበት ማህበረሰብ የስብዕናችንን መሰረተ ድንጋይ ያስቀምጣል፡፡ መጥፎ ማህበረሰብ ተዓምራዊ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ምሉዕ ስብዕና ያላቸውን ግለሰቦችን ለአገር አያበረክትም፡፡ ‹‹ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር…›› እንድሉ በክፉ መንጋ መሀል ያሉ ጥቂት ግብረገብ ግለሰቦችም መልካምነታቸው ሲበከል አይቆይም፡፡ ስለዚህ ለሙስና አወንታዊ አመለካከት ባለው ማህበረሰብ ውስጥ ፈፅሞ ሙስናን መዋጋትና ድል ማድረግ አይቻልም፡፡ ብልሹ አሰራርን ለመዋጋት ብልሹ ባህልን ማስወገድ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ የሚሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ሙስናን መዋጋት ባህልን ከማደስ ይጀምራል፡፡›› ሙስናን በነውርነት የሚፈርጅ ባህል ስንገነባ ያኔ ከሙስና የፀዳ አሰራር ሰፍኖ እናያለን፡፡
ሙስና በሁሉም ሃይማኖቶች የተወገዘ እኩይ ተግባር ነው፡፡ ለአብነት ያክል ከሙሴ ህግ ጀምሮ ሙስና የተከለከለ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ከክርስትና እስከ እስልምና ሃይማኖት ያሉ አስተምህሮቶችን ብናይ ሙስና ሃጢያትና ሀራም መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ መንፈሳዊነት ቦታውን ለቁሳዊነት ሲለቅ የሙስና ዛፍ ያንሰራፋል፡፡ የሰው ልጅ አዕምሮና አስተሳሰብ እንዳይዝግ የሚከላከለው ሰውኛ ሞራሊቲም ላይመለስ ይኮበልላል፡፡
ሙስናን ህጋዊ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ብቻ ልንከላከለው አንችልም፡፡ ፀረ-ሙስና ኮሚሽንም ብቻውን ለውጥ አያመጣም፡፡ በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የልማት ድርጅቶች እና የግል ድርጅቶች ደረጃ ቀርቶ በግለሰብ ደረጃ የግለሰቦች የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ቢቋቋም ከንቱ ልፋት ነው፡፡ ሙስናን ለመከላከል ዋነኛ መሳሪያው የግለሰቦች አስተሳሰብ ላይ መስራትና ሙስናን የሚፀየፍ ባህል መፍጠር ነው፡፡
ሙስናና ብልሹ አሰራር ከአዕምሮ ዝገት የሚመነጭ ማህበረሰባዊ በሽታ ስለሆነ የዝገት መከላከያው ደግሞ ግብረገብ የሆነ ትውልድ መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ገንዘብ አምላኪ ትውልድ ባለበት አገር ህሊና ዳኝነቱን ለሆድ ይለቃል፡፡ መጨረሻውም ተባብሮ አገርን መዝረፍና የራስን ጥቅም ማሯሯጥ ነው፡፡ ለብሄራዊ ጥቅም ሳይሆን ለግል ጥቅም ማሰብ የአስተሳሰቦች ሁሉ የበላይ ይሆናል፡፡ ‹‹ሰርቶና ለፍቶ ማግኘት›› ሳይሆን ‹‹አጭበርብሮ ሃብትን ማጋበስ›› እንደ ጀግንነት ይቆጠራል፡፡ ጉዳይ ለማስፈፀም ‹‹በእግር ሳይሆን በእጅ መጓዝ›› አማራጭ የሌለው አማራጭ ሆኖ ይመጣል፡፡ ያኔ ‹‹ምን ታውቃለህ ሳይሆን ማንን ታውቃለህ እና ምን ይዘህ መጣህ›› ትባላለህ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን መሬት አልባ የሆነ ወጣት አርሶ አደር የመሬት ኮሚቴዎችን ስንዝር የምታክል መሬት እንኳን ስጡኝ ብሎ ይጠይቃቸውና እነሱም ለውለታቸው ጉቦ መክፈል እንዳለበት ይነግሩታል፡፡ ስለ ጉቦ ሲነሳ በሁኔታው የተናደደው ወጣት ያንጎራጎራት ዜማ ትዝ አለችኝ፡፡
በሬውን አረዱት አርሶ ´ሚያበላውን፤
ላሚቱን አረዷት ጥጃ ´ምትወልደውን፤
ማረድስ ኮሚቴን ጉቦ ´ሚበላውን፡፡
በጣም የሚያሳዝነው ነገር የአገር ሀብት በሙሰኞች ሲመዘበር ‹‹አይተን እንዳላየ›› የምናልፈው ብዙዎች መሆናችን ነው፡፡ ማህበረሰባችን ‹‹ዝምታ ወርቅ ነው›› ይልሀል፡፡ እኔ ግን እልሀለሁ ‹‹ወርቁ ከብሄራዊ ባንክ ሲዘረፍ›› እያየህ ዝም ብትል ዝምታህ እንኳን ወርቅ ሊሆን የነሀስ ዋጋም አያወጣልህ፡፡
ሙስና የአገር እድገት ነቀርሳ ነው፣ መልካም መስተዳደርን ያዳክማል፣ የኢኮኖሚ አቅምን ያዳሽቃል፣ ፍትህን ያዛባል፣ የእኩልነት ሚዛንን ያበላሻል፣ ሰብዓዊ ክብርን ይንዳል፣ ህዝብን ጦም ሊያሳድርም ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ሙስና ሰደድ እሳት ነው አገርን ያቃጥላል፡፡ ስለዚህ መንግስታዊ (ልማታዊ) ሌቦችን ወልዶ ማሳደግ መቅረት አለበት፡፡
ሲሾም የበላ አፈር ይብላ፡፡ ‹‹ውጉዝ ከወ አርዮስ ፡፡››
ደርብ ተፈራ
(የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ባልደረባ እና የፓለቲካል ሳይንስ ምሩቅ)

No comments:
Post a Comment